Since 2014 E.C
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በአዋጅ ቁጥር 74/2014 ዓ.ም በከተማው ውስጥ ያሉ የተለያዩ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችን የማስተዳደር እና የማሳደግ ሁለንተናዊ ኃላፊነት ተሰጥቶት የተቋቋመ መንግስታዊ የልማት ድርጅት ነው። በዚህም መሠረት ኮርፖሬሽኑ መናፈሻዎችን ወይም ፓርኮችን፣ አደባባዮችን፣ ፕላዛዎችን ወይም የፌስቲቫል ሜዳዎችን እና ዙ ፓርኮችን ያስተዳድራል። የኮርፖሬሽኑ ዋና ትኩረት ነባር የመዝናኛ ቦታዎችን በማስተዋወቅ ከሚሰጣቸው አገልግሎት ገቢ በማመንጨት የመዝናኛ ቦታዎችን ማሻሻል፣ ማስፋፋትና ማልማት ነው።