የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
 ENG  /     አማ   /    oro  

ብሔረ ጽጌ ፓርክ

የሚገኙበት ቦታ መረጃ

  •         በንፋስ ስልክ ላፍቶ  ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው አደይ አበባ አካባቢ  የሚገኝ ነው፡፡

ለምቶ አገልግሎት የሰጠበት ጊዜ

  •        የብሄረ ጽጌ ፓርክ ተብሎ የሚጠራው በአጼ ሐይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት በ1957 ዓ.ም በአቶ ስብሀቱ በተባሉ ግለሰብ የለማ ሲሆን በለውጡ ወደ መንግስት ይዞታነት ተዛውሮ በአሁኑ ወቅት በከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ስር ሆኖ ለነዋሪው የመናፈሻ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
  •           ብዙ ዓመታትን አገልግሎት ቢሰጥም በጫና ምክንያት አንዳንድ ግንባታዎች የተጎዱ እና እርጅና ይታይበታል፡፡

ልዩ የሚያደርገው

  •      በውስጡ የመካነ እንስሳት ማቆያ ፤የተለያዩ የችግኝ ማበዣ ግሪን ሀውስና ችግኝ ጣቢያ፣ በፋሲል ግንብ አምሳያ የተሰራ ባለአንድ ፎቅ ህንጻ አብዛኛው ዛፎቹ ሀገር በቀል መሆናቸው፣50 ዓይነት የአዋፍት ዝርያዎች እና ጦጣዎች በመሃሉ አቋርጦ የሚያልፍ ትንሹ አቃቂ ወንዝ መኖሩ እና መልክዓ-ምድራዊ ገጽታው ልዩ የሆነ ተፈጥሮአዊ ውበት ያለው ነው፡፡

የልማት ሁኔታው

 

  •        ለመናፈሻ አገልግሎት እንዲሁል ተጨማሪ ግንባታዎች እና መሰረተ ልማቶች የተሰሩለት ቢሆንም ከይዞታ ማረጋገጫ ካርታው በቀር ስለ ልማቱን የሚገልጽ ምንም ዓይነት ሳይት ፕላን የለውም፡፡
  •        ፓርኩ ሲመሰረት የተሰራ የውሃ ማጠራቀሚያ ኩሬ  ቢኖርም አገልግሎት እየሠጠ አይገኝም፤ተጨማሪ እድሳት ቢደረግለት የፓርኩን የውሃ ፍላጎት ሊያሟላ ይችላል፡፡
  •     የስሪ ፌዝ መብራ ቆጣሪ እና መስመር አለው፡፡
  •     የውስጥ ለውስጥ የእግረኛ መንገድ  የቴራዞ እንዲሁም የኮፕል ስቶን መንገድ እና ፓርኪንግ ቦታ  አለው፡፡
  •     በውስጡ ለፓርኩ አገልግሎት የሚውል አነስተኛ ችግኝ ጣቢያ አለው፡፡
  •     ከተጠቃሚው አንጻር በቂ ያልሆነ የመጸዳጃ ቤቶች አሉት፡፡

የአስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታው   

  •      ፓርኩ ተዋረድ ያለው የተሟላ የፓርክ አስተዳደር መዋቅር ያለው ቢሆንም ነገር ግን  አትልክተኞች፣ካሸሮች እና ጥበቃዎች በቋሚነት በቢሮው ተቀጥረው እየሠሩ ይገኛል፡፡

 የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

  • ለሰርግ፤ለልደት እና ሌሎች የመዝናኛ አገልግሎት በደረሰኝን ክፍያ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
  • የበር መግቢያ ክፍያ 10 ብር  በትኬት እየተከፈለ የጉብኝት አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል፡፡
  •    የእንስሳት ጉብኝት አገልግሎት፡፡
  • የፓርኩ አረንጓዴ ቦታ ደረጃውን የጠበቀ ውብ እና ማራኪ ነው፡፡

 


Addis Ababa City Administration Public Recreational Areas Corporation


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን


BULCHIINSA MAGAALAA FINFINNEE Korporeeshinii Bulchiinsa Iddoowwan Bashannanaa ummataa


ስልክ : +251-913558544 / +251-934471822 / +251-934471822
አድራሻ : አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ