የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
 ENG  /     አማ   /    oro  

አፍሪካ ፓርክ

በተለምዶ አፍሪካ ፓርክ ተብሎ አፍሪካ፣ ኢትዮጵያ ፓርክ ከ30ዓመት በፊት በሚድሮክ ግሩፕ ለምቶ በ2011 ዓ.ም ለአዲስ አብሮ ባ ከተማ አስተዳደር ተሰጠ።  የሚጠራው በጠቅላላ ሶስት ፓርኮችን ያካተተ ሲሆን እነርሱም አፍሪካ ፓርክ፣ኢትዮጵያ ፓርክ እና አዲስ ፓርክ ናቸው፡፡ስለሆነም ፓርኮቹ የሚገኙበት ሁኔታ እንደሚከተለው ተዳስሷል፡፡

 

የሚገኙበት ቦታ መረጃ

  • በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው በውጪ ጉዳይ ሚንስትር ፊት መንገድ አካፋይ ላይ የሚገኝ ነው፡፡

 

ለምቶ አገልግሎት የሰጠበት ጊዜ

  •  በሼህ አሊ አላሙዲ ሙሀመድ ወጪ በ1997 ዓ.ም ዲዛይን ተዘጋጅቶ ደረጃውን ጠብቆ የለማ ሲሆን እያስተዳደር አገልግሎት እንዲሰጥ በ2011 ዓ.ም ለቢሮው ተላልፎ ለነዋሪው የመዝናኛ አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል፡፡
  •  ብዙ ዓመታትን አገልግሎት ባለመስጠቱ በጫና ምክንያት ባለመጎዳቱ አዲስ ነው ለማለት ይቻላል፡፡

 

ልዩ የሚያደርገው

  • በአፍሪካ ፓርክ የመጀመሪያው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የመሰረቱ የአፍሪካ መሪዎች እና የአፍሪካ ህብረትን የመሰረቱ የአፍሪካ መሪዎች የተከሏቸው ታሪካዊ ቅርስ የሆኑ ዛፎች የሚገኙበት ነው፡፡

 

የልማት ሁኔታው 

  • ፓርኩ ሲለማ ደረጃውን የጠበቀ ዲዛይን የተዘጋለት ሲሆን ልማቱን የሚገልጽ ሳይት ፕላን አለው፡፡
  •  ፓርኩ 3 ኢንች የውሃ ቆጣሪ ቢኖረውም ሊኬጅ ስላለው ከፍተኛ የውሃ ክፍያ ያስወጣል
  • የመብራት ቆጣሪ ክፍያ ባለመፈጸሙ መብራት ተቆርጧል፡፡
  •  የውስጥ ለውስጥ የንጣፍ ዲንጓይ መንገድ አዲስ ፓርክ በዛፍ ስር በመፈንቀሉ ጥገና ያስፈልገዋል፡፡
  •  የመጸዳጃ ቤቶች የውሃ ቧንቧዎች እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው መተካት እና መጠገን ይጠይቃሉ፡፡

 

የአስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታው

  •  እንደሌሎች ፓርኮች ተዋረድ ያለው የተሟላ የፓርክ አስተዳደር መዋቅር የለውም ሆኖም ግን  አትልክተኞች፣ካሸሮች እና ጥበቃዎች በቋሚነት በቢሮው ተቀጥረው እየሠሩ ይገኛል፡፡
  •  በአትክልተኞች የማይሸፈነው የፓርኩ አረንጓዴ ቦታ ለጥቃቅን እና አነስተኛ 2 ማህበራት ለአንድ ዓመት ጊዜ በሚታደስ ውል ተሰጥቷቸው እየተንከባከቡ ይገኛሉ፡፡
  •  1 ካፍቴሪያ እና 1 የፈጣን ምግብ መሸጫ ሱቅ አውትሶርስ ተደርጎ አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል፡፡

 

 የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

  •   በሶስቱም ፓርኮች በቢሮው በታተመ ቲኬት የልጆች መጫወቻ  አገልግሎት
  • ለሰርግ፤ለልደት እና ሌሎች የመዝናኛ አገልግሎት በደረሰኝን ክፍያ የሚሰጥ አገልግሎት
  • የመግቢያ በር ክፍያ 100 ብር  በትኬት
  •  የሁሉንም ፓርኮችን  ደህንነት ለማስጠበቅ በመግቢያ በሮች የጥበቃ ሠራተኞች ተሟልተው ስራቸው እያከናወኑ መሆናቸው፡፡
  •  የፓርኩ አረንጓዴ ቦታ ደረጃውን የጠበቀ ውብ እና ማራኪ ነው፡፡

 


Addis Ababa City Administration Public Recreational Areas Corporation


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን


BULCHIINSA MAGAALAA FINFINNEE Korporeeshinii Bulchiinsa Iddoowwan Bashannanaa ummataa


ስልክ : +251-913558544 / +251-934471822 / +251-934471822
አድራሻ : አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ