የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
+251-913558544 / +251-934471822 / +251-934471822
Info@AACAPRAC.gov.et
አ.አ.ከ.አ.ህ.መ.ቦ.አ.ኮ
መነሻ
ፓርኮች
እንጦጦ ፓርክ
አፍሪካ ፓርክ
አዲስ-ዙ ፓርክ | 6 ኪሎ አንበሳ ግቢ
ሃምሌ 19 ፓርክ
ኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ
ብሔረ ጽጌ ፓርክ
ኢትዮ ኮርያ ዘማቾች መታሰቢያ ፖርክ
አምባሳደር ፓርክ
ከንቲባ ወ/ጻዲቅ ፓርክ
ልደታ መናፈሻ (መዋኛ ገንዳ)
ብሎግ / ዜና
ማስታወቂያ
ክፍት የስራ ቦታ
ጨረታ
ስለ እኛ
አግኙን
ENG /
አማ /
oro
English
አማርኛ
Afaan oromoo
ብሔረ ጽጌ ፓርክ
የሚገኙበት ቦታ መረጃ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ
ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው አደይ አበባ አካባቢ
የሚገኝ ነው፡፡
ለምቶ አገልግሎት የሰጠበት ጊዜ
የብሄረ ጽጌ ፓርክ ተብሎ የሚጠራው በ
አጼ ሐይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት በ1957 ዓ.ም በአቶ ስብሀቱ በተባሉ ግለሰብ የለማ ሲሆን በለውጡ ወደ መንግስት ይዞታነት ተዛውሮ በአሁኑ ወቅት በከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ስር ሆኖ ለነዋሪው የመናፈሻ አገልግሎት እየሰጠ
ይገኛል፡፡
ብዙ ዓመታትን አገልግሎት ቢሰጥም በጫና ምክንያት አንዳንድ ግንባታዎች የተጎዱ እና እርጅና ይታይበታል፡፡
ልዩ የሚያደርገው
በውስጡ የመካነ እንስሳት ማቆያ ፤የተለያዩ የችግኝ ማበዣ ግሪን ሀውስና ችግኝ ጣቢያ፣ በፋሲል ግንብ አምሳያ የተሰራ
ባለአንድ ፎቅ ህንጻ
አብዛኛው ዛፎቹ ሀገር በቀል መሆናቸው፣50 ዓይነት የአዋፍት ዝርያዎች እና ጦጣዎች በመሃሉ አቋርጦ የሚያልፍ ትንሹ አቃቂ ወንዝ መኖሩ እና መልክዓ-ምድራዊ ገጽታው ልዩ የሆነ ተፈጥሮአዊ ውበት ያለው ነው፡፡
የልማት ሁኔታው
ለመናፈሻ አገልግሎት እንዲሁል ተጨማሪ ግንባታዎች እና መሰረተ ልማቶች የተሰሩለት ቢሆንም ከይዞታ ማረጋገጫ ካርታው በቀር ስለ ልማቱን የሚገልጽ ምንም ዓይነት ሳይት ፕላን የለውም፡፡
ፓርኩ ሲመሰረት የተሰራ የውሃ ማጠራቀሚያ ኩሬ
ቢኖርም አገልግሎት እየሠጠ አይገኝም፤ተጨማሪ እድሳት ቢደረግለት የፓርኩን የውሃ ፍላጎት ሊያሟላ ይችላል፡፡
የስሪ ፌዝ መብራ ቆጣሪ እና መስመር አለው፡፡
የውስጥ ለውስጥ የእግረኛ መንገድ
የቴራዞ እንዲሁም የኮፕል ስቶን መንገድ እና ፓርኪንግ ቦታ
አለው፡፡
በውስጡ ለፓርኩ አገልግሎት የሚውል አነስተኛ ችግኝ ጣቢያ አለው፡፡
ከተጠቃሚው አንጻር በቂ ያልሆነ የመጸዳጃ ቤቶች አሉት፡፡
የአስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታው
ፓርኩ ተዋረድ ያለው የተሟላ የፓርክ አስተዳደር መዋቅር ያለው ቢሆንም ነገር ግን
አትልክተኞች፣ካሸሮች እና ጥበቃዎች በቋሚነት በቢሮው ተቀጥረው እየሠሩ ይገኛል፡፡
የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
ለሰርግ፤ለልደት እና ሌሎች የመዝናኛ አገልግሎት በደረሰኝን ክፍያ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
የበር መግቢያ ክፍያ 10 ብር
በትኬት እየተከፈለ የጉብኝት አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል፡፡
የእንስሳት ጉብኝት አገልግሎት
፡፡
የፓርኩ አረንጓዴ ቦታ ደረጃውን የጠበቀ ውብ እና ማራኪ ነው፡፡
Addis Ababa City Administration Public Recreational Areas Corporation
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን
BULCHIINSA MAGAALAA FINFINNEE Korporeeshinii Bulchiinsa Iddoowwan Bashannanaa ummataa
ስልክ : +251-913558544 / +251-934471822 / +251-934471822
አድራሻ : አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ