በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ቦታው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አጠገብ የሚገኝ ነው፡፡
ቀደም ሲል ለአብዮቱ እና ለኩባ ሰማዕታት መታሰቢያነት በደርግ ዘመነ መንግስት ትግላችን ሀውልት በሚባል የለማ ሲሆን በ2009 ዓ.ም በቢሮው የማሻሻያ እድሳት ተከናውኖለት ለነዋሪው የመዝናኛ አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል፡፡
ልዩ የሚያደርገው
የኢትዮ-ኩባ የወዳጅነት ፓርክ በውስጡ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ትግል እና በኢትዮ-ሱማሌ ጦርነት ከኢትዮጵያ ጎን ቆመው የተሰው የኩፓ ወታደሮች ታሪክ የሚዘክሩ ቅርሶች የሚገኙበት ነው፡፡