የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
 ENG  /     አማ   /    oro  

ስለ እኛ

የኮርፖሬሽኑ ተግባርና ኃላፊነት

1.    የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች፣ የዱር እንሳስት ዙ-ፓርኮች፣ ፕላዛዎች እና የክብረ በዓል አደባባዮችን ተረክቦ መጠበቅ፤ መንከባከብ፤ ማስተዳደር፤ 

2.    ነባር መዝናኛ ቦታዎችን እና  ዙ-ፓርኮችን ማሰፋፋት፣ እድሳት ማድረግ፣ ማልማት፣ ማስገንባት፤ 

3.    የኩነት ዝግጅት አገልግሎት በመስጠት በቂ ገቢ በማመንጨት ቀጣይነት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ፤

4.    የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለተጠቃሚው ማስተዋወቅ እና የገበያ ልማት ስራዎችን በመስራት ጎብኚዎችን መሳብ፤

5.    የዱር እንስሳትን መንከባከብ፣ የጤና አጠባበቅና በሽታ መከላከል፣ አመጋገብና አኗኗር ሁኔታ መከታተል፤ አዳዲስ የዱር እንስሳት ወደ ፓርኮቹ እንዲገቡ ማድረግ፤ 

6.    እጽዋትን በሳይንሳዊ ዘዴ መሰረት በማልማት እና በመንከባከብ የመዝናኛ ፓርኮች ገጽታ ውብና ማራኪ ማድረግ፤ 

7.    የተጎዱ ፓርኮችን የገጸ-ምድር ላንድስኬፕ ዲዛይን በማዘጋጀት የማደስ ስራ መስራት፤

8.    የተጠቃሚውን ፍላጎት ለማሟላትና የቦታዎችን ደረጃ ለማሻሻል የሚያግዙ የጥገና እና የተጨማሪ አገልግሎት መስጫዎች ግንባታ ሥራ መስራት፤

9.    የፓርኮችን እጽዋትና እንስሳት ብዙሀ-ህይወት በመጠበቅ ጥናትና ምርምር ማካሄድ፤ ስልጠና እና ትምህርታዊ አገልግሎት መስጠት፤ 

 

ኮርፖሬሽኑ የሚያስተዳድራቸዉ መዝናኛ ስፍራዎች 


1)    አዲስ ዙ ፓርክ 
2)    ሐምሌ 19 ፓርክ፤
3)    ብሔረ ጽጌ ፓርክ፤
4)    ኢትዮ ኩባ ወዳጅነት ፓርክ፤
5)    ኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ፓርክ፤
6)    አፍሪካ፣ ኢትዮጵያ እና አዲስ አበባ ፓርኮች፤
7)    ከንቲባ ወ/ጻዲቅ ፓርክ፤
8)    አምባሳደር ፓርክ፤ 
9)    ልደታ መናፈሻ (መዋኛ ገንዳ)፤
10)     እንጦጦ ፓርክ ናቸዉ፡፡

 

ኮርፖሬሽኑ የሚሰጣቸው አገልግሎት ዓይነቶች

1)    የመናፈሻ አገልግሎት (በሁሉም ዕድሜ ክልል ለሚገኙ በግል እና በቡድን ለሚመጡ ሰዎች)፤
2)    የዙ ፓርክ አገልግሎት መስጠት፤
3)    በከፊል ወይም በሙሉ የመዝናኛ ቦታዎችን/ፓርኮችን ማከራየት፤
4)    የተለያዩ መዝናኛ/መጫወቻ ፋሲሊቲ አገልግሎት (የህጻናት መጫወቻ፣ ለወጣቶችና ለአዋቂዎች የሚሆኑ)
5)    ለተለያዩ ሁነቶች(ኢቬንቶች) የሚሆን ቦታ ማከራየት (ለሰርግ፣ ልደት፣ የቡድን ቆይታ፣ ወዘተ)፤
6)    ሁነቶች/ኢቬንቶችን ማዘጋጀት፤
7)    የአዳራሽ፣ ሱቆች እና የመዝናኛ ቤቶች ማከራየት፤

 

የእኛ ተልዕኮ

የከተማዋ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች፣ መናፈሻዎች፣ ዙ-ፓርኮች፣ የህዝብ አደባባዮች እና ፕላዛዎችን በመጠበቅ፣ በመንከባከብ፣ ብዝሀ-ሕይወትን በመጠበቅ፣ በቴክኖሎጂ በመታገዝ የአገልግሎቱን ጥራትና ዓይነት በማሳደግ ለጎብኚዎች ዘመናዊ እና ምቹ በማድረግ የህብረተሰቡን የመዝናኛ ፍላጎት በማርካት ገቢ ማመንጨት፡፡

የእኛ ራዕይ

በ2022 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች በሚሰጡት አገልግሎት ስታንዳርድ፣ ጥራት እና ዓይነት ከአስሩ የአፍሪካ ከተማ ፓርኮች ተመራጭ ሆነው ማየት፡፡