የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን የ2016 የግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ ። ክንውኑ በሁሉም ዘርፍ አበረታች እና ለበለጠ ውጤት የሚያነሳሳ መሆኑ ተገለጸ።
ባለፉት 6 ወራት በኮርፖሬሽን ስር የሚገኙ የመዝናኛ ቦታዎችን መሰረተ ልማት የማሻሻል፣ በስታንዳርዱ መሰረት የማስዋብ እና የማልማት፣ ፖርኮችን በውበት ሰጭ አበቦች እና እጸዋት የማስዋብ ፣በየፖርኩ እጸዋቶችን መንከባከብ ፣በራስ አቅም ችግኝ ማዘጋጅት፣የዱር እንስሳትን እንክብካቤ እና ጤና አጠባበቅን ማሻሻል ፣የኢኮቱሪዝም እና የደንበኞች አገልግሎት ማሻሻል እና የጎብኚዎችን ቁጥር ማሳደግ ፣በራስ አቅምና በጋራ ሁነት ማዘጋጅት ወዘተ ላይ የተለየ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን እና ጥሩ ውጤት መመዝገቡን፤ይሄው ጥሩ አፈጻጸም በቀጣይነት የበለጠ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገ የውይይቱ ተሳታፊዎች ገልጿዋል።
በመጨረሻም የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስኬያጅ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ "ያሳለፍነው 6 ወር እቅድ አፈጻጸም በሁሉም ዘርፍ አበረታች እና አዳጊ መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም በግማሽ አመቱ ውስጥ ታቀደው ያልተከናወኑ አንዳንድ ተግባራት በቀጣይ 6 ወር እቅዳችን ውስጥ አካተን እስካሁን ካደረግነው ጥረት በላይ ጠንክረን በመስራት የበጀት አመቱን እቅድ 100 % ለማሳካት በትጋት መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል "በማለት የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።
በህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን የእጽዋት ልማት እና እንክብካቤ ዳይሬክቶሬ...
post date 2024-01-05 23:47:23 - Read Moreበ23/5/2016 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ...
post date 2024-02-03 13:03:59 - Read Moreየህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን "ከእዳ ወደ ምንዳ "በሚል ርእስ ለአጠቃላይ ...
post date 2024-02-03 13:05:12 - Read More